የመንግሥቱ ኩሞ አዶሼ መልዕክት
የይርጋለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን
|
እንኳን ወደ ይርጋዓለም ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ ዌብ ሳይት ገጽ በደህና መጡ ፡፡ ይ/ዓለም ፖሊ ቴ/ኮሌጅ በኢትዮጵያ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በመሀከላዊ ሲዳማ ዞን ዋና ከተማ በሆነችዉ በዉብቷ ይርጋዓለም ከተማ የሚገኝ ኮሌጅ ስሆን ከሀዋሳ 47 ኪ.ሜ ሪቀት ላይ ይገኛል፡፡ |
|
ኮሌጃችን ከተመሰረተበት 1994 ዓ/ም አንስቶ ለበርካታ ዜጎች መደበኛ፤አጫጭር ስልጤና እና የኢንዱስትሪ ኤክስተንሽን የድጋፍ አገልጎሎት ለኢንተርፕራይዞች እየሰጠ የሚገኝ ኮሌጅ ነዉ፡፡ ኮሌጁ በአሁኑ ጊዜ በአዲሱ ቴክንክና ሙያ ፖሊሲ (TVT Policy) መሰረት የአካባቢዉን ጸጋ መነሻ አድርጎ በስምንት(8) የስልጠና ዓይነቶች መደበኛና አጫጭር ስልጤናዎችን በመስጠት የሰለጤነ የሰዉ ኃይል በይ/ዓለም የተቀናጀ ኢንዳስትር ፓርክ ለሚገኙ ፋብርካዎች በቅርበት እያቀረበ ያለ እንድሁም በክልላችን እና በሀገርቱ የሰለጤነ የሰዉ ሃይል ፍላጎትንም እያሟላ ይገኛል፡፡ ኮሌጁ ዘመኑ የሚጠይቀዉን መሰረተ ልማት በማሟላት ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለዉን ቅንጅት በማጠናከር የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እየተወጣ የሚገኝ ስሆን አሁን ካለበት በተሻለ ሁነታ የዉስጥ ገቢዉንም በማሳደግ እና ለህብረተሰቡ የተሻለዉን አገልግሎት ለመስጤት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ከወትሮዉ በተሻለ ሁነታ በመቀናጀት ለመስራት እና ለለዉጥ ቆርጦ የተነሳበት ጊዜ በመሆኑ አብሮን ለሚሰራ ማንኛዉም መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ካልሆነ አካላት ጋር ለመስራት በራችን ክፍት መሆኑን እየገለጽኩ ኮሌጃችንን መርጠዉ ስለጎበኙ እና ገንብ የሆነ አስተያየቶዉን ስለሰጡን እንድሁም አብሮን ለመሥራት፤ መረጃ ለማግኜት እና ለጥናትና ምርምር የሚረዱ መረጃዎችና ከዌብሳይት ገጻችን ለማግኜት ስለመረጡን በእራሴና በኮሌጁ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁኝ፡፡ መንግሥቱ ኩሞ አዶሼ የይ/ዓለም ፖሊ ቴ/ኮሌጅ ዲን |