የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ማኔጅመንት አባላት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ከጉብኝት በመቀጠል እስካሁን የተደረገው ድጋፍና ክትትል ግብረ _ መልስ፣ የቀሪ ወራት ዕቅድና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከዞኑ አመራሮች ከወረዳና ከተማ አመራሮችጋር ውይይት አካሂዷል ።
ሀዋሳ:ግንቦት 26/2017 የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ተግባራት በታቀደው መሠረት ለማስፈጸም የዜጎች ኑሮ ለማሻሻል የተለየ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በሁለት ዘመቻ ድጋፍ ስደረግ መቆየቱን ገልፀው ዛሬ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በበጀት ዓመት ውስጥ የተደረገው ድጋፍ ግብረ መልስ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት መደረጉንና በቀጣይ ወር በሚሰሩ ቀሪ ተግባራት ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የስራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ አፈጻጸምና ጥራትን በተመለከተ ፣ የአንድ ማዕከል ግንባታ አፈጻጸም ፣ ዜጎችንና ኢንተርፕራይዞችን በባዮሜትሪክስ ምዝገባ አፈጻጸም ፣ ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ስልጠና አፈጻጸም ፣ የቴ/ሙያ ኮሌጆች የሠልጣኞች ቅበላ ፣ በዲጂታላይዜሽን ስራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጓል።
በተለያዩ ተግባራት ላይ በዞኑ የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን ገልፀው አንዳንድ ወረዳዎች ላይ የሚታዩ ዝቅተኛ አፈጻጸሞች በቀጣይ መሻሻል እንዳለባቸው ተነስቷል።
ዛሬ የተደረገው ጉብኝትና ውይይት ወረዳዎች እርስ በርስ ተሞክሮዎችን የተለዋወጡበት መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረዋል ።
በሌላም በኩል የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት መደረግ እንዳለበት ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የዞኑ አስተባባሪዎች የወረዳና ከተማ አስተዳዳሪዎችና የዘርፉ አመራሮች የተገኘውን የተሻለ አፈጻጸም ለማስቀጠልና ድክመቶችን ለማረም በቁጭት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።